ገለፃ
«የኢስላም መልዕክተኛ የሆኑት ሙሐመድ የአላህ ሶላት እና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን» የሚለው መጽሐፍ የነቢዩ ሙሐመድን (የአላህ ሶላት እና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘራቸውን፣ አስተዳደጋቸውን፣ የተባረከው ትዳራቸውን፣ የወሕይ አወራረድን፣ የመጨረሻ መልዕክታቸው አጀማመርን ጨምሮ ስለ ህይወታቸው የሚያብራራ መጽሐፍ ነው። በተጨማሪም የነቢይነታቸውን ተአምርና የእውነተኝነታቸውን ምልክትም ይገልፃል። እንዲሁም: ይዘውት የመጡት ሸሪዓ የሰው መብት እንዲጠበቅ እና እንዲከበር የነበረውን ሚናም ያብራራል። እርሳቸውን የተቃረኑ አካላት በርሳቸው ላይ የነበራቸውን አቋም እና ለርሳቸው የሰጡትን ምስክርነትም ለሰዎች መሪ እና ስለ ፈጣሪ አሃዳዊነት ተጣሪ ያደረጋቸውን የላቀ ስብዕና ከመተንተን ጋር የሚቀርብበት መጽሐፍ ነው።
ሌሎች ትሩጓሜዎች 54