×
New!

Bayan Al Islam Encyclopedia Mobile Application

Get it now!



እስልምና የአላህ መልክተኞች ሃይማኖት ነው።

እስልምና ማለት አጽናፈ ዓለሙን ለፈጠረውና ላስተናበረው አላህ በመውደድና በማላቅ እጅ መስጠትና መታዘዝ ማለት ነው። የእስልምና መሰረቱ በአላህ ማመን ነው። እርሱ ፈጣሪ መሆኑን፤ ከርሱ ውጪ ያሉት ባጠቃላይ ፍጡር መሆናቸውን ማመን፤ እርሱ ብቸኛ አምልኮ የሚገባውና አጋር የሌለው መሆኑንና ከርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ ማመን ነው።

እስልምና ከርሱ ውጭ ያለው ሃይማኖት አላህ ከሰዎች የማይቀበለው የሆነ ብቸኛው ሃይማኖት ነው። እስልምና ሁሉም ነቢያቶች ሰላም ይስፈንባቸውና ይዘውት የመጡት ሃይማኖት ነው።

ከእስልምና መሰረቶች መካከል በሁሉም መልዕክተኞች ማመን እና አላህ ትእዛዙን ለባሮቹ እንዲያስተላልፉ መልእክተኞችን እንደላከ እና መጽሐፎችን እንዳወረደላቸው ማመን ነው። የመጨረሻው መልዕክተኛም ሙሐመድ ሰላም ይስፈንባቸውና ናቸው። ከርሳቸው በፊት የነበሩትን የመልክተኞች ህግጋት በሚሽርና በመለኮታዊ ህግ ልኳቸዋል። በታላላቅ ተዓምራትም አግዟቸዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቁ የዓለማት ጌታ ንግግር የሆነው የተከበረው ቁርኣን ነው። የሰው ልጅ ካወቀው መጽሐፍ በሙሉ ትልቁ መፅሀፍ ነው። በይዘቱ፣ በቃላቱ እና በአደረጃጀቱ ሁሉ ተአምራዊ ነው። በውስጡም ወደ ሐቅ የሚመራና ለዱንያም ሆነ ለመጨረሻው ዓለም ደስታ የሚያደርስ የሆነን መመርያ ይዟል። እስከ ዛሬ ድረስም በወረደበት ዐረብኛ ቋንቋ ተጠብቆ ይገኛል። ከርሱም አንድ ፊደል እንኳ አልተለወጠምም፣ አልተቀየረምም።

በመላዕክቱ ማመንና በመጨረሻው ቀን በዕለተ ትንሳኤ ሰዎች እንደሰሩት ስራ አይነት ሊመነዳቸው ዘንድ ሰዎችን ከየመቃብራቸው እንደሚቀሰቅሳቸው ማመንም ከእስልምና መሰረቶች ናቸው። አማኝ ሆኖ ስራውም መልካም የሆነ ሰው ጀነት ውስጥ ዘላቂ ፀጋ አለለት፤ የካደና ስራው ክፉ የሆነ ደሞ እሳት ውስጥ ከባድ ቅጣት አለለት። በጎም ይሁን መጥፎ አሏህ በፃፈው ቀደር ማመንም ከእስልምና መሰረቶች መካከል አንዱ ነው።

ሙስሊሞች ዒሳ የአላህ ባሪያ እና መልዕክተኛው እንደሆኑ ያምናሉ። የአላህ ልጅ እንዳልሆኑም ያምናሉ። አላህ ታላቅ ነውና ሚስትም ልጅም ሊኖረው አይችልም። ነገር ግን አላህ በቁርኣን ውስጥ ለኢየሱስ በርካታ ተዓምራትን የሰጣቸው ነብይ እንደሆኑ እና አላህን ምንም ሳያጋሩበት በብቸኝነት እንዲያመልኩ ህዝቡን እንዲጠሩ አላህ የላካቸው መሆናቸውን ነግሮናል። ኢየሱስ ሰዎች እንዲያመልኳቸው አልጠየቁም ይልቁንም እራሳቸውም ፈጣሪያቸውን ያመልኩ እንደነበር ነግሮናል።

እስልምና ከጤነኛ ተፈጥሮና አእምሮ ጋር የሚስማማ፣ የተስተካከሉ ነፍሶች የሚቀበሉትና ታላቁ ፈጣሪ ለፍጡራኑ የደነገገው ሃይማኖት ነው። ለሁሉም ሰው ባጠቃላይ የመልካም እና የደስታ ምንጭ የሆነ ሃይማኖት ነው። አንዱን ዘር ከአንዱ ዘር ወይም አንዱን ቀለም ከአንዱ ቀለም አይለይም። እስልምና ውስጥ ሰዎች እኩል ናቸው። በእስልምና ውስጥ ማንም ከሌላው በመልካም ስራው መጠን ካልሆነ በስተቀር አይለይም።

ማንኛውም አይምሮ ያለው ሰው ሁሉ በአላህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ መልዕክተኛነት የማመን ግዴታ አለበት። ይህ ደግሞ ለሰው አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ምክንያቱም አላህ በትንሳኤ ቀን ለመልእክተኞቹ ስለሰጠው መልስ ይጠይቀዋልና። አማኝ ከሆነ ለርሱ ትልቅ ድልና ስኬት አለለት፤ ከሓዲ ከሆነ ደግሞ ለርሱ ግልጽ ኪሳራ ይጠብቀዋል።

ወደ እስልምና ሃይማኖት መግባት የፈለገ ሰው ትርጉሟን አውቆና አምኖባት እንዲህ ማለት ነው የሚጠበቅበት: "አሽሃዱ አን ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአሽሃዱ አነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ" (ትርጉሟም: ከአሏህ በቀር በእውነት ሊመለክ የሚገባው አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ እንደሆኑ እመሰክራለሁ ማለት ነው።) በዚህም ሙስሊም ይሆናል። ቀጥሎ አላህ ግዴታ ያደረገበትን ለመተግበር የተቀሩትን የእስልምና ድንጋጌዎች አንድ በአንድ መማር ይጠበቅበታል።

ለተጨማሪ መረጃ: https://byenah.com/am/discover-islam


Index

እስልምና የአላህ መልክተኞች ሃይማኖት ነው። 3

معلومات المادة باللغة العربية